የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ከአለምአቀፋ የህፃናት አድን ድርጅት /unicef / ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ለተከታታይ ቀናት በሚሰጠው የስልጠና መርሀግብር ላይ የሀብት አስተዳደር ፣ ክፍያ ፣ ጨረታ እና ሌሎችም ወጪዎች ላይ አንድ ወጥ የሆነ ግንዛቤ በመጨበጥ ውጤታማ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከuncief የመጡት አቶ ኢዮብ ጌታቸው ገልፀዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ የረድኤት ድርጅቶች ጋር በትብብር በመስራት የታቀደውን የልማት ስራ ወደ መሬት ለማውረድ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዋች የማየረተካ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱም ሀላፊው አስረድተዋል፡፡ በ unicef በጀት በዞን ደረጃ እና በየወረዳው የሚከናወኑ የልማት ተግባራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲተገበሩ ያልተቆጠበ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ አቶ ኢዮብ አስታውቀዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች ተጨማሪ እውቀት አግኝተው ውስን የሆነውን የህዝብ እና የመንግስት በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባ አቶ ኢዮብ አሳስበዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የUN ፕሮግራሞች አስተባባሪ አቶ ጥላሁን አዳነ unicef በተለያዩ በዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ በሚያደርገው ድጋፍ የመጡ ተጨባጭ ለውጦችን አድንቀዋል። አቶ ጥላሁን አክለውም ተጠያቂነት ያማከለ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር በመሆኑ ግልፀኝነትን እንደሚያሰፍን ስለ ስልጠናው ውጤቶች በተናገሩበት ወቅት ገልፀዋል። ተሳታፊዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰቡት አቶ ጥላሁን የተሻለ አቅም እንደሚፈጥርላቸውም ጠቁመዋል። ተግባር ተኮር የሆነው ስልጠና በኮምፒውተር የታገዘ የልምምድ ሂደቶችን ተከትሎ እንደሚቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን እና ሚድያ ግንኙነት ዘግቧል። During the training sessions, Ato Dereje elaborated on the critical role of preventing and controlling corruption to uphold the rule of law and promote transparency and accountability. He stressed the need for concerted efforts to strengthen institutional mechanisms for combating corruption and ensuring adherence to ethical standards across all levels of government. By equipping participants with essential knowledge and tools for promoting ethical conduct and good governance, the Addis Ababa City Administration Finance Office aims to foster a culture of integrity, responsibility, and effectiveness in public service delivery. Through continuous training and awareness initiatives, the office endeavors to uphold the highest ethical standards and promote the well-being of the community.